ዳያስፖራው የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት በማሳደግ ሂደት ላይ ከፍ ያለ ተሳትፎ እንዲያደርግ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጥሪ አቀረቡ
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) ጥር 3/2014
ዳያስፖራው የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት በማሳደግ ሂደት ላይ ከፍ ያለ ተሳትፎ እንዲያደርግ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጥሪ አቅርበዋል።
አምባሳደር ሬድዋን በኢንቨስትመንት ኮሚሽን አማካኝነት በተዘጋጀው የዳያስፖራ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
በወቅቱም ዳያስፖራው ማህበረሰብ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ ሂደት ላይ በኢንቨስትመንት ዘርፉ ከፍ ያለ ተሳትፎ እንዲኖረው አምባሳደር ሬድዋን ጥሪ አቅርበዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ ላይ የተደረገውን ያልተገባ ጫና በመቃወም ትልቅ ፖለቲካዊ ውጤት እንዲገኝ ዳያስፖራው ላደረገው ብሄራዊ ተጋድሎ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን አሁን ወቅቱ ሀገሪቱን በኢኮኖሚ የምንደግፍበት ስለሆነ የተጠናከረ ትብብር ሊደረግ እንደሚገባ ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ በወጀብ ውስጥ ቀጥ ብላ እንድትሄድ ተፅዕኗችሁ የጎላ ነበር ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው አሁንም በትብብር የሀገራቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር በጎ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መሰራት አለበት ብለዋል።
በዚህ ረገድ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል በዲፕሎማሲው ዘርፍ የታየው አንድነት አብነት በመሆኑ ዳያስፖራው በኢንቨስትመንቱ ላይ ተሳታፊ ከመሆኑ ባሻገር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንዲያድግ ሀገሪቱ ያላትን ሀብት በሚገባ የማስታዋወቅ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
አምባሰደር ሬድዋን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ሀገራችንን ካላላቀቅን ፖለቲካዊ ፍላጎታችንና ሀገራዊ ጥቅማችንን ማስጠበቅ አይቻልም ያሉ ሲሆን ከዚህ ለመላቀቅም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት አለብን ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሌሊሴ ነሜ በበኩላቸው ዳያስፖራው በሀገሩ መዋለ ነዋዩን እንዲያፈስና የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት አቅም በማስተዋወቅ የላቀ ሚና እንዲጫወቱ መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ዛሬ በተከፈተው የዳያስፖራ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ በርካታ ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች መሰል ገለጻዎችን በሚኒስትሮቻቸው አማካኝነት አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ኢትዮጵያን በዘላቂነት እናልማ!
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
በዮቱብ
https://www.youtube.com/channel/UC9lAZ1l0TvJG65R-QeCDHkg
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/Amnaddistv
በቴሌግራም
https://t.me/addismedianetwork
በትዊተር
https://twitter