ዲያስፖራው የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ከፍ ያለ ተሳትፎ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ጥር 3/2014 (ዋልታ) ዲያስፖራው የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት በማሳደግ ሂደት ላይ ከፍ ያለ ተሳትፎ እንዲያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጠየቁ።

በኢንቨስትመንት ኮሚሽን አማካኝነት የተዘጋጀ የዲያስፖራ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ዲያስፖራው በኢንቨስትመንቱ ላይ ተሳታፊ ከመሆኑ ባሻገር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንዲያድግ አገሪቱ ያላትን ሀብት በሚገባ የማስታዋወቅ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አሳስበዋል፡፡

ከኢኮኖሚ ጥገኝነት አገሪቱን ካላላቀቅን ፖለቲካዊ ፍላጎታችንና አገራዊ ጥቅማችንን ማስጠበቅ ስለማይቻል ከዚህ ለመላቀቅም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት አለብን ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በበኩላቸው ዲያስፖራው በሀገሩ መዋለነዋዩን እንዲያፈስና የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት አቅም በማስተዋወቅ የላቀ ሚና እንዲጫወቱ ጠይቀዋል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://www.facebook.com/waltainfo
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!

ዲያስፖራው የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ከፍ ያለ ተሳትፎ እንዲያደርግ ተጠየቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *